ለዘመን ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

Print

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የወረቀት አክሲዮኖች  ወደ ኤሌክትሮኒክ አክሲዮኖች መቀየር እንዳለባቸው  ባወጣው መመሪያ እና በታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ኢካገባ/621/17 በተጻፈ ደብዳቤ  ባሳወቀን  መሰረት የመቀየር ሂደቱን ለማሳካት የሚረዱ የባለአክሲዮኖቻችንን መረጃ እየሰበሰብን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤት በተሰጠን መመሪያ መሰረት፡-

 

1.  ዕድሜያቸው  5 ዓመት እና ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ  ባለአክሲዮኖች ወላጆች ወይም ሞግዚቶች የህጻናቱን   የብሔራዊ መታወቂያ በማቅረብ  ንድታስመዘግቡ፡፡

2.  ድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ባለአክሲዮኖች   ወላጆች  ወይም ሞግዚቶች የራሳችሁን  ብሔራዊ መታወቂያ በማቅረብ እንድታስመዘገቡ ፡፡

3.  አክሲዮን በጋራ የያዛችሁ ባለአክሲዮኖች ከመካከላችሁ አንዱን በመወከል እና የተወካዩን መረጃ (ማለትም የተወካዩን ብሔራዊ መታወቂያ እና አድራሻ ) በባለአክሲዮን መዝገብ ላይ እንድታስመዘግቡ፡፡

4.  እድሮች እና ማህበራት አግባብነት  ባላው የመንግስት መዝጋቢ አካል የተመዘገባችሁበትን ስርተፍኬት እና  የምዝገባ መለያ ቁጥር ይዛችሁ በመቅረብ እንድታስመዝግቡ፡፡

5.  ሁሉም ባለአክሲዮኖች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራችሁን (TIN) እንድታስመዘግቡ

በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ማንኛዉንም አይነት የአክሲዮን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉት ከላይ የተጠቀሱትን ሲያሟሉ መሆኑን እየገለፅን መረጃችሁን በሁሉም የዘመን ባንክ ቅርንጫፎች ወይም አዲስ አበባ ከተማ ፣ ሰንጋ ተራ በሚባለው አካባቢ ውስጥ  በሚገኘው የባንኩ  ዋና መስሪያ ቤት 15ኛ ፎቅ አክሲዮን ክፍል በመቅረብ እንድታስመዘግቡ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ፡

የፋይናንስና ኢንቨስተርስ ግንኙነት መምሪያ

 በስልክ ቁጥር 011-5-54-00-53 ደውለው ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለዘመን ባንክ አ.ማ