የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

የዘመን ባንክ አ.ማ.

የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባ  ጥሪ

ለተከበራችሁ የዘመን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች

በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣367(1) እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን  ማኅበሩ የተሻሻለው  የመመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 12.1፣12.5 ፣13  እና አንቀጽ 14.1 መሠረት የዘመን ባንክ .. የባለአክሲዮኖች 17 መታዊ መደበኛ እና 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 1 ቀን 2018 .. ከጠዋቱ 200 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጠቅላላ ጉባዔው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

 

1.  ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች

·         የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና /ቤት አድራሻ - አዲስ አበባልደታ ክፍል ከተማ፣ወረዳ 07 የቤ/ቁ አዲስ

·         የባንኩ ድረገጽ ፡ https://www.zemenbank.com

·         የአክሲዮን ማኅበሩ ምዝገባ ቁጥር - KK/AA/3/0002009/2005

·         የአክሲዮን ማበሩ ስም - ዘመን ባንክ አ.ማ

·         የአክሲዮን ማበሩ አይነት- በባንክ ሥራ የተሰማራ 

·         የአክሲዮን ማኅበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ - 14,985,602,000.00

·         የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ - 9,542,948,000.00

 2. የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

  1. የተተኪ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሹመት ማጽደቅ፤
  2. እስከ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅና ሪፖርቱን ተቀብሎ ማጽደቅ፤
  3. እ.ኤ.አ. የ2024/25 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  4. እ.ኤ.አ. የ2024/25 በጀት ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥና በቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  5. እ.ኤ.አ. ከ2019/20 ጀምሮ በየዓመቱ ከሚከፋፈለው ትርፍ ላይ 3 በመቶ በልዩ መጠባበቂያ ሂሳብ ሲቀመጥ የነበረው የመጠባበቂያ ገንዘብ ከ2024/25 ጀምሮ እንዲቋረጥና የተጠራቀመው ገንዘብ ለባለአክሲዮኖች እንዲከፋፈል በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤

 

  1. እ.ኤ.አ. በ2024/25 በጀት ዓመት በተገኘ የተጣራ ትርፍ አደላደል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤

7.  እ.ኤ.አ. ከ2025/26 እስከ 2027/28 በጀት ዓመት ድረስ የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና ክፍያቸውን መወሰን፤

  1. እ.ኤ.አ. የ2024/25 ለዳይሬክተሮች ቦርድ ከተጣራ ትርፍ ላይ የሚታሰብ ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያ መወሰን፤
  2. እ.ኤ.አ. የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበል መወሰን፤
  3. የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የምልመላ መስፈርትና የምርጫ አሠራር ረቂቅ መመሪያ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤

 

3. የባለአክሲዮኖች 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

1.  ጥቅምት 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በ11ኛው የባንኩ ባለአክሲዮኖች አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የባንኩ ካፒታል እንዲያድግ ሲወሰን የመጨረሻ የመክፍያ ቀን ሰኔ 23 ቀን 2020 ዓ.ም ተብሎ የተቀመጠውን ውሳኔ ማሻሻል፤

2.  የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤

  1. የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል

 

ማሳሰቢያ

·         በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት በባንኩ ዋና /ቤት 15ተኛ ፎቅ በሚገኘው ፋይናንስ እና ኢንቨስተርስ ግንኙነት መምሪያ በአካል በመቅረብ  ለዚሁ ዓላማ በባንኩ በተዘጋጀው የውክልና መስጫ ቅጽ ላይ በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን ፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በባንኩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በኢትዮያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 20/3/ መሰረት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ሠራተኞች በማናቸውም የባለአክሲዮኖች ጉባዔ ላይ ማንኛውንም ባለአክሲዮን ወክለው መገኘት አይችሉም፡፡

 

·         የባንኩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ዜግነታቸዉ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

 

·         የባንኩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻያ የባንኩ የዳይይሬክተሮች ቦርድ አባላት የምልመላ መስፈርትና የምርጫ አሠራር ረቂቅ መመሪያን ከባንኩ ድረገጽ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

·         ለተጨማሪ መረጃ ሰንጋ ተራ ፣ ራስ አበበ አረጋይ ዳና በሚገኘው የባንኩ ዋና /ቤት 15 ፎቅ፣ ፋይናንስ እና ኢንቨስተርስ ግንኙነት መምሪያ በአካል መቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 115 54 00 53/66 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የዘመን ባንክ ..

 የዳይሬክተሮች ቦርድ